Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 20:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሣራንም፣ “እነሆ፤ ለወንድምሽ ለአብርሃም አንድ ሺሕ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ፤ ይህም በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና ዐብረውሽ ያሉ ሁሉ እንዲያውቁት ነው፤ በዚህም ንጽሕናሽ ይረጋገጣል” አላት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሣራንም “አንቺ ምንም አስነዋሪ ተግባር ያልፈጸምሽ ንጹሕ መሆንሽን ከአንቺ ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲረዱት ምልክት ይሆን ዘንድ ለወንድምሽ ለአብርሃም አንድ ሺህ ብር ሰጥቼዋለሁ” አላት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሣራ​ንም አላት “እነሆ፥ ለወ​ን​ድ​ምሽ አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብር ሰጠ​ሁት፤ ይህም ለፊ​ትሽ ክብር ይሁ​ንሽ፤ በሁ​ሉም እው​ነ​ትን ተና​ገ​ራት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሣራንም አላት እነሆ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዓይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 20:16
11 Referencias Cruzadas  

ግልጽ ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።


‘እኅቴ ናት’ ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርሷም ደግሞ ራስዋ፥ ‘ወንድሜ ነው’ ብላኛለች፥ ይህንን በቅን ልብ እና በንጹሕ ኅሊና ነው ያደረግሁት”።


ሎሌውንም፦ “ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው?” አለችው።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።


የመርከቡ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥ አምላክህን ጥራ፥ ምናልባትም እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን ይሆናል” አለው።


የሚሰማን ጆሮ የሚገሥጽ ጠቢባዊ ምክር፥ እንደ ወርቅ ጉትቻ እንደሚያንጸባርቅም ዕንቁ ነው።


ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።


አቢሜሌክም ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህን ሰው ሚስቱንም የሚነካ ሞትን ይሙት” ብሎ አዘዘ።


አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባርያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios