ዘፍጥረት 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎሌውም፦ “ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ልመልሰውን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩም፣ “ሴቲቱ ከእኔ ጋራ ወደዚህ ምድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆን ምን አደርጋለሁ? ልጅህን አንተ ወደ መጣህበት አገር ልውሰደውን?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዩም “ምናልባት የምመርጥለት ሴት ከእኔ ጋር ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገውን?” ብሎ ጠየቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውም፥ “ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ ሀገር ከእኔ ጋር ለመምጣት ባትወድድስ ልጅህን ወደ መጣህበት ሀገር ልመልሰውን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውም፦ ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ለመልሰውን? አለው። |