ዘፍጥረት 24:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፥ አገነነውም፥ በጎችንና ላሞችን፥ ብርንም፥ ወርቅንም፥ ወንዶች ባርያዎችንና ሴቶች ባርያዎችን፥ ግመሎችንም፥ አህዮችንም ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ እርሱም በልጽጓል፤ በጎችና ከብቶች፣ ብርና ወርቅ፣ ወንድና ሴት አገልጋዮች፣ ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፥ የፍየልና የከብት መንጋ፥ ብርና ወርቅ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው አገነነውም፤ በጎችንና ላሞችን፥ ብርንም፥ ወርቅንም፥ ወንዶም ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን ግመሎችንም አህዮችንም ሰጠው። |
በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት።
ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
ሰውነትን አካላዊ እንቅስቃሴ ማለማመድ መጠነኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም እንኳ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት የተስፋ ቃል ስላለው፥ ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።