ዘፍጥረት 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን፥ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤ እንዲሁም ከዋክብትን ፈጠረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ቀንን እንዲመግብ፥ ትንሹ ብርሃንም ከከዋክብት ጋር ሌሊትን እንዲመግብ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ። |
ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በክህሎቱ ብርታት አንድ እንኳ አይጎለውም።
ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል፥ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን የማይዛነፍ ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ፥ እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ ጌታ እንዲህ ይላል፦
“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።
ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ፥ ጌታ አምላካችሁ ከሰማይ በታች ላሉት ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸውን፥ ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንም፥ የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ፥ በመሳት እንዳትሰግዱላቸውና እንዳታመልኳቸው ተጠንቀቁ።