ገላትያ 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የጸና ኪዳን፥ የሰው ስንኳ ቢሆን፥ ማንም አያፈርሰውም ወይም አይጨምርበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! እስቲ ይህን ነገር በሰው ዘንድ ከተለመደ ነገር ጋር አነጻጽሩት፤ አንድ ሰው የገባው ቃል ኪዳን እንኳ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሰው ሊሽረው ወይም ሊጨምርበት አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እንናገራለን፤ ሰውም እንኳን የጸናውን ኪዳን አይንቅም አይጨምርበትምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የሰው ስንኳ ቢሆን እርግጠኛውን ኪዳን ማንም አይንቅም ወይም አይጨምርበትም። |
ወንድሞች ሆይ! በሌሎቹ ሕዝቦች እንዳገኘሁት በእናንተም ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳቀድሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።
ነገር ግን ዐመፃችን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያጎላ ከሆነ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በቁጣ ቢቀጣን ትክክል አይደለም ሊባል ነውን? እንደ ሰው እላለሁ።
ከሥጋችሁ ደካማነት የተነሣ እንደ ሰው አነጋገር እናገራለሁ። የሰውነታችሁን ክፍሎች ሕገ ወጥነትን ለሚያመጣ ለርኩሰትና ለሕገ ወጥነት ባርያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ ስለዚህ አሁን የሰውነታችሁን ክፍሎች ቅድስና ለሚያመጣ ለጽድቅ ባርያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።