የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
ዕዝራ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ ወደሚገኝበት ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደን እንደ ነበር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን በታላላቅ ድንጋዮች እየገነቡና ቅጥሩንም በወፍራም ምሰሶዎች እየሠሩ ነው፤ ሥራው በትጋት በመከናወንና በእነርሱም አመራር በመፋጠን ላይ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ይሁዳ ምድር ሄደን የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ በድንጋይና በጠርብ እንጨት ሲሠራ ማየታችን ለግርማዊነትዎ የታወቀ ይሁን፤ ሥራውም በሽማግሌዎቹ መሪነት በጥንቃቄና በፍጥነት እየተሠራ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በጥሩ ድንጋይ ይሠራል፤ በቅጥሩም ውስጥ ልዩ እንጨት ይደረጋል፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፤ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል። |
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ።
ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።