እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ አሳፍንና ወንድሞቹን፥ ዖቤድ-ኤዶምንም፥ ስልሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን በዚያ በጌታ ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
ዕዝራ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አከበሩ፤ እንደ ሥርዓቱም የዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በዕለቱ በቍጥር አቀረቡ፤ የዕለቱን ነገር በዕለቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለእያንዳንዱ ቀን እንደ ታዘዘው፣ በሚያስፈልገው ቍጥር ልክ የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ የዳስ በዓልን በተጻፈው መሠረት አከበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕጉም በሚያዘው መሠረት የዳስ በዓልን አከበሩ፤ ለእያንዳንዱም ቀን የተመደበውን መሥዋዕት አቀረቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዓቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ። |
እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ አሳፍንና ወንድሞቹን፥ ዖቤድ-ኤዶምንም፥ ስልሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን በዚያ በጌታ ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
በትውልዳቸው ከተቈጠሩት በቀር ዕድሜያቸው ሦስት ዓመት የሆናቸውና ከዚያ በላይ የሆኑ በየሰሞናቸውም ለሥራቸውና ለአገልግሎታቸው ዕለት ዕለት ወደ ጌታ ቤት ለሚገቡ ወንዶች ሁሉ፤
“እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ቁርባን ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም ለመጠጥም ቁርባን፥ ለአንድነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለጌታ አቅርቡ።