ንጉሥ ሰሎሞን የጌታ ቤት ሁሉንም ሥራ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለጌታ ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፥ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በጌታ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው።
ዕዝራ 2:69 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህ ምናን ብር፥ አንድ መቶ የካህናት ልብስ እንደየአቅማቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ለቤተ መቅደሱ ሥራ ማከናወኛ የሚችሉትን ያኽል አዋጥተው ያቀረቡት ስጦታ ሲደመር አምስት መቶ ኪሎ ወርቅ፥ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ኪሎ ብር ሆነ፤ ለካህናቱም የሚሆን አንድ መቶ የካህናት ልብስ ሰጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። |
ንጉሥ ሰሎሞን የጌታ ቤት ሁሉንም ሥራ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለጌታ ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፥ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በጌታ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው።
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለጌታ ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ በሚዛንም የማይመዘን ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም በዚያ ላይ ጨምርበት።
ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክሊት ብር፥ ዐሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።
ከአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶች፥ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤት በመጡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው እንዲሠራ በፈቃዳቸው መባ ሰጡ።