ሕዝቅኤል 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለ ሰይፍ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ለራስህ ትወስደዋለህ፥ በራስህና በጢምህም አሳልፈው፥ ሚዛንንም ውሰድ ጠጉሩንም ትከፋፍለዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተም፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ የተሳለ ሰይፍ ወስደህ እንደ ጢም መላጫ ጠጕርህንና ጢምህን ተላጭበት፤ ጠጕሩንም በሚዛን ከፋፍል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የተሳለ ሰይፍ ወስደህ ጢምህንና የራስ ጠጒርህን በሙሉ ተላጭ፤ ጠጒርህንም በሚዛን መዝነህ በሦስት ቦታ ክፈለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚላጭ ምላጭ ይልቅ የተሳለ ጐራዴን ውሰድ፤ ወስደህም በእርስዋ ራስህንና ጢምህን ተላጭ፤ ሚዛንንም ውሰድ፤ ጠጕሩንም ትከፋፍለዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለን ጐራዴ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ወደ አንተ ትወስደዋለህ፥ ራስህንና ጢምህንም ትላጭበታለህ፥ ሚዛንንም ውሰድ ጠጕሩንም ትከፋፍላለህ። |