ሕዝቅኤል 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም ገመድ አደርግብሃለሁ፥ የምትከበብበትንም ቀኖች እስክትፈጽም ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው ጎንህ አትገላበጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከበባህን ወራት እስክትፈጽም ድረስ ከአንዱ ጐን ወደ ሌላው መገላበጥ እንዳትችል በገመድ አስርሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበባው እስኪፈጸም ድረስ ከአንድ ጐንህ ወደ ሌላው እንዳትዘዋወር በገመድ አስርሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም ገመድ አደርግብሃለሁ፤ የምትከበብበትንም ወራት እስክትፈጽም ድረስ ከጎን ወደ ጎንህ አትገላበጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ገመድ አደርግብሃለሁ፥ የምትከበብበትንም ወራት እስክትፈጽም ድረስ ከጐድን ጐድንህ አትገላበጥም። |
አንተም ለራስህ ስንዴና ገብስ፥ ባቄላና ምስር፥ ማሽላና አጃን ውሰድ፥ በአንድ ዕቃ ውስጥ አድርጋቸው፥ ለራስህም ምግብ አዘጋጅ፥ በጎንህ እንደ ምትተኛበት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ።
የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።