La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምትመገበውም ምግብ በሚዛን በየቀኑ ሃያ ሰቅል ይሁን፥ በየጊዜውም ትበላለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በየቀኑ የምትበላውን እህል ሃያ ሃያ ሰቅል መዝነህ አስቀምጥ፤ በተወሰነ ጊዜ ትበላዋለህ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በየቀኑ 230 ግራም የሚመዝን ምግብ ትወስዳለህ፤ እርሱም እስከሚቀጥለው ቀን እንዲበቃህ በማድረግ በተወሰነ ሰዓት ትመገበዋለህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ት​በ​ላ​ውም በሚ​ዛን በየ​ቀኑ ሃያ ሃያ ሰቅል ይሁን፤ በየ​ጊ​ዜው ትበ​ላ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምትበላውም በሚዛን በየቀኑ ሀያ ሀያ ሰቅል ይሁን፥ በየጊዜው ትበላዋለህ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 4:10
9 Referencias Cruzadas  

እነሆ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፉንና ርዳታውን፤ የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤


በዓናቶትም ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፥ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ምግብህን በድንጋጤ ብላ፥ ውኃህንም በመንቀጥቀጥና በስጋት ጠጣ፤


የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር ባለመታመን በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እጄን እዘረጋባታለሁ፥ የምግቧንም በትር እሰብራለሁ፥ ራብን እሰድድባታለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ አጠፋለሁ፤


ውኃም በልክ ትጠጣለህ፥ የኢን መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ ትጠጣለህ፥ በየጊዜውም ትጠጣለህ።


ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ እኔ በኢየሩሳሌም የምግብን በትር እሰብራለሁ፥ ምግብ እየፈሩ በሚዛን ይበላሉ፥ ውኃም እየደነገጡ በልክ ይጠጣሉ፤


አንድ ሰቅል ሀያ ጌራህ ይሆናል፤ ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል እና ዐሥራ አምስት ሰቅል ሲጨመር፥ አንድ ምናን ይሁንላችሁ።


የእንጀራችሁንም በትር በሰበርሁ ጊዜ፥ ዐሥር ሴቶች እንጀራችሁን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው ዳግመኛ እንጀራችሁን ያመጡላችኋል፤ ትበላላችሁም ነገር ግን አትጠግቡም።