ሕዝቅኤል 39:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እመልስሃለሁ፥ እመራሃለሁ፥ ከሰሜን ዳርቻ አወጣሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች እወስድሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ እንዲሁም እጐትትሃለሁ፤ ከሩቅ ሰሜን አምጥቼ በእስራኤል ተራሮች ላይ እሰድድሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቅጣጫውን አስለውጬ ሩቅ ከሆነው ከሰሜን አገር ገፋፍቼ በእስራኤል ተራራዎችም ላይ እንዲዘምት አደርገዋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሰበስብሃለሁ፤ እመራሃለሁ፤ ከሰሜንም ዳርቻ አወጣሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች እወስድሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እመልስሃለሁ፥ እነዳህማለሁ፥ ከሰሜንም ዳርቻ እጐትትሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ። |
የሰሜን አለቆች ሁሉ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኃይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሃት አፍረዋል፥ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱት ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።
በስተ ሰሜን ርቆ ከሚገኘው ስፍራህ አንተ፥ ከአንተም ጋር ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ ብዙ ሕዝብ፥ ታላቅ ጉባኤና ብርቱ ሠራዊት ጋር ሆነህ ትመጣለህ።
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ አሁንም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥