ሕዝቅኤል 36:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎችን፥ ሕዝቤን እስራኤልን፥ በእናንተ ላይ አስሄዳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሱሻል ርስትም ትሆኛቸዋለሽ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ልጅ አልባ አታደርጊአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችን፣ ሕዝቤን እስራኤልን በእናንተ ላይ እንዲመላለሱ አደርጋለሁ፤ ይወርሷችኋል፤ እናንተም ርስታቸው ትሆናላችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ አልባ አታደርጓቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! እንደገና በምድሪቱ መኖር ትችሉ ዘንድ መልሼ አመጣችኋለሁ፤ ምድሪቱም እንደገና ተመልሳ የራሳችሁ ትሆናለች፤ ዳግመኛም ልጆች አልባ አትሆንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎችንም፥ ሕዝቤን እስራኤልን በእናንተ ላይ አበዛለሁ፤ እነርሱም ይወርሱአችኋል፤ ርስትም ትሆኑአቸዋላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ ልጅ አልባ አታደርጓቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎችንም፥ ሕዝቤን እስራኤልን፥ በእናንተ ላይ አስሄዳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይወርሱሻል ርስትም ትሆኛቸዋለሽ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ልጅ አልባ አታደርጊአቸውም። |
ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና በብንያም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች፥ በደጋውም ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ፥ ምስክሮችንም ጠርተው በውሉ ሰነድ ላይ ፈርመው ያትሙታል፥ ይላል ጌታ።”
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከሕዝቦች አወጣቸዋለሁ፥ ከአገሮች እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾች አጠገብ፥ በምድሪቱም መኖሪያ በሚሆኑ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
በመልካም ማሰማርያ አሰማራቸዋለሁ ጋጣቸውም በእስራኤል ተራሮች ከፍታ ላይ ይሆናል፤ በዚያ በመልካም ጋጣ ውስጥ ይመሰጋሉ፥ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ ማሰማርያ ይሰማራሉ።
ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች አወሩ እንዲህም አሉ፦ “እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርሷም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው።