ሕዝቅኤል 34:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኛ በተበተኑት መንጋዎቹ መካከል ሳለ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጨለማ ቀን፥ ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኛ ከመንጋው ጋራ ሳለ፣ የተበተኑበትን በጎች እንደሚፈልግ ሁሉ፣ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ። በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበግ እረኞች ከተበታተኑት በጎቻቸው መካከል መንጋዎቻቸው እንደሚፈለጉ፥ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበታተኑበት ቦታ ሁሉ አድናቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደመናና በጭጋግ ቀን እረኛ ከበጎቹ መካከል የተለየውን እንደሚፈልግ፥ እንደዚሁ በጎችን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጭጋግ ቀን ከተበተኑባቸው ሀገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ፥ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ። |
ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?
ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።
አሕዛብ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል” በሉ።
እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዓይነ ስውርና አንካሳው ያረገዘችና ምጥ የያዛትም በአንድነት ይሆናሉ፤ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።
“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ባድማ ሆና፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ በሆነችው በዚህች ስፍራ፥ በከተሞችዋም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉ የእረኞች መኖሪያ ስፍራ ዳግመኛ ይኖራል።
ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዷል፥ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሠራዊት ጌታም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በውጊያ ላይ ክብር እንደተቀዳጀ ፈረስ ያደርጋቸዋል።
በዚያም ቀን አምላካቸው ጌታ ሕዝቡን እንደ መንጋ ያድናቸዋል፤ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ያበራሉ።