Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልጋቸዋለሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋቸዋለሁ፤ እጠብቃቸዋለሁም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በጥንቃቄም እጠብቃቸዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በጎ​ችን እሻ​ለሁ፤ እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 34:11
24 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።


እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፥ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባርያህን ፈልገው።


ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስክር መዝሙር።


እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርሷ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።


እኔ እራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትከናወንለታለች።


የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፥ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ስለምን ትፈራለህ?


ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፦ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ ይላል።


የመንጋዬንም ትሩፍ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ራሴ ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ፥ ይበዛሉም።


እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዓይነ ስውርና አንካሳው ያረገዘችና ምጥ የያዛትም በአንድነት ይሆናሉ፤ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፥ ከተበተናችሁባቸው አገሮችም እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።


ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፥ አገሮችም እያዩ በመካከልሽ ፍርድን አመጣብሻለሁ።


እንዲህም በል፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮች፥ ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ።


እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔ ራሴ ነጥቄ እሄዳለሁ እወስዳለሁም፥ ሊያድንም የሚችል ማንም የለም።


እኔ ደግሞ በቁጣ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።


ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዷል፥ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሠራዊት ጌታም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በውጊያ ላይ ክብር እንደተቀዳጀ ፈረስ ያደርጋቸዋል።


በዚያም ቀን አምላካቸው ጌታ ሕዝቡን እንደ መንጋ ያድናቸዋል፤ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ያበራሉ።


የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና፤” አለው።


መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል።


ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ማምጣት ይገባኛል፤ ድምፄንም ይሰማሉ፤ አንድም መንጋ ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos