እነሆ፥ አንተ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ ነህ፥ ከአንተ የተሰወረ ምሥጢር የለም።
ከዳንኤል ይልቅ ጠቢብ ነህን? ከአንተስ የተሰወረ ምስጢር የለምን?
ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ የሆንክ ይመስልሃል፤ ምንም ምሥጢር እንደማይሰወርብህም ታስባለህ፤
ከዳንኤል ይልቅ አንተ ጥበበኛ ነህን? ብልሃተኞችም በጥበባቸው አላስተማሩህም።
እነሆ፥ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ ነህ፥ ምሥጢርም ሁሉ ከአንተ የተሸሸገ አይደለም።
እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጠ፤ ሊተረጉምላት የተሳነውና ከእርሱ የተሰወረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም።
የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን? ጥበብን የግልህ ለማድረግ ትመኛለህን?
ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤
ኖኅ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ በውስጧ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ።