| ሕዝቅኤል 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ኖኅ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ በውስጧ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስቱ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።Ver Capítulo አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እነዚህ ሦስቱ ሰዎች ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም በመካከልዋ ቢኖሩ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።Ver Capítulo |