ሕዝቅኤል 27:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደሴቶች የሚኖሩ ሁሉ በአንቺ ደንግጠዋል፥ ነገሥታቶቻቸውም እጅግ ፈርተዋል፥ ፊታቸውም ተለውጦአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጠረፍ አገር የሚኖሩ ሁሉ፣ በአንቺ ሁኔታ ተደናገጡ፤ ንጉሦቻቸው በፍርሀት ራዱ፤ ፊታቸውም ተለዋወጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በባሕር ጠረፍ የሚኖሩ ሁሉ አንቺን ከገጠመሽ መጥፎ ዕድል የተነሣ ደንግጠዋል፤ ንጉሦቻቸውም እንኳ ሳይቀሩ ተሸብረዋል፤ በያንዳንዳቸውም ፊት ላይ ፍርሀት ይነበባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደሴቶች የሚኖሩ ሁሉ አለቀሱልሽ፤ ነገሥታቶቻቸውም እጅግ ፈርተዋል ፊታቸውንም ነጭተው አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደሴቶች የሚኖሩ ሁሉ ተደንቀውብሻል፥ ነገሥታቶቻቸውም እጅግ ፈርተዋል ፊታቸውም ተለውጦአል። |
ብዙም ሕዝቦች አንተን አይተው እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ ሰይፌንም በፊታቸው ባወዛወዝሁ ጊዜ ነገሥታቶቻቸው ይንቀጠቀጣሉ፤ በወደቅህበትም ቀን እያንዳንዱ ስለ ነፍሱ በየጊዜው ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።