ሕዝቅኤል 26:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፈረሶቹ ኮቴዎች ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረጋግጣል፥ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽ ምሰሶዎች ወደ መሬት ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዶችሽ ሁሉ በፈረሶቹ ኰቴ ይረጋገጣሉ፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ታላላቅ ምሰሶዎችሽ ወደ ምድር ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራዊቱ በፈረሶቹ ሰኰናዎች መንገዶችሽን ይረጋግጣል፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ጠንካራ ዐምዶችሽም ወደ መሬት ይወድቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሶቹ አደባባይሽን ይረግጣሉ፤ ሠራዊቶችሽንም በሾተል ይገድሏቸዋል፤ የጸና አርበኛሽንም በምድር ላይ ይጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፈረሶቹ ኮቴ ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረመርማል፥ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽም ሐውልት ወደ ምድር ይወድቃል። |
በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።
ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።