ሕዝቅኤል 25:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣ ከተሞላበት ቅጣት ጋር ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ፥ በቀሌን በእነሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በመዓቴም እቀጣቸዋለሁ፤” በምበቀላቸውም ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣ ከተመላ ቅጣቴ ጋር ታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በእነርሱም ላይ በምወስደው እርምጃ እኔ እግዚአብሔር መሆን ያውቃሉ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመዓት መቅሠፍትም ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ፤ በቀሌንም በላያቸው በአደረግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመዓት መቅሠፍትም ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ፥ በቀሌንም በላያቸው ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ እንደሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ በዓባይ ወንዝ ያለውን ውኃ በእጄ ባለው በትር እመታለሁ፥ ወደ ደምም ይለወጣል።
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እንደ ቁጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ላይ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።