ሕዝቅኤል 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ እንዲህ በላት፦ አንቺ ያልነጻሽ፥ በቁጣም ቀን ያልዘነበብሽ ምድር ነሽ በላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ምድሪቱን፣ ‘አንቺ ያልነጻሽ በቍጣም ቀን ዝናብ ያላገኘሽ ምድር ነሽ’ በላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! ምድራቸው ስለ ረከሰች በቊጣዬ ዝናብ እንዳይዘንብ በማድረግ ልቀጣት የተዘጋጀሁ መሆኑን ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ! አንቺ ዝናም የማይዘንብብሽ፥ በቍጣ ቀን ጠል የማይወርድብሽ ምድር ነሽ በላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፦ አንቺ ያልነጻሽ በቁጣም ቀን ያልዘነበብሽ ምድር ነሽ በላት። |
አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።
በርኩሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ መዓቴን በአንቺ ላይ እስክጨርስ ድረስ ከእንግዲህ ወዲያ ከርኩሰትሽ ንፁህ አትሆኚም ምክንያቱም አነጻሁሽ ነገር ግን ንፁህ አልሆንሺምና።