ሕዝቅኤል 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትልልቅ ክንፎችና ብዙ ላባ ያለው ሌላ አንድ ትልቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም ይህ ወይን እንዲያጠጣው ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ፥ ቅርንጫፉንም ከተተከለበት ከመደብ ወደ እርሱ ሰደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ደግሞም ትልቅ ክንፍ ያለውና አካሉ በላባ የተሸፈነ ሌላ ታላቅ ንስር ነበር። ያ የወይን ተክልም ውሃ ለማግኘት ከተተከለበት ቦታ ሥሩን ወደ እርሱ ሰደደ፤ ቅርንጫፉንም ወደ እርሱ ዘረጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንዲሁም ታላላቅ ክንፎችና ብዙ ላባዎች ያሉት ሌላ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ አሁን እንግዲህ የወይን ተክሉ ሥሮቹንና ቅርንጫፎቹን ወደ ንስሩ ዘረጋ፤ ይህንንም ያደረገው ከተተከለበት መደብ ውሃ ያጠጣው ዘንድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ታላቅ ክንፍና ብዙ ጽፍርም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ፤ እነሆም ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ ሰደደ፤ ሐረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ አዘነበለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቅ ክንፍና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም፥ ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ። |
ንጉሡንም በጠላቱ ላይ እንዲያግዝ፥ በታላቅ ኃይል ወደ ጦርነት የሚወጣ፥ በትእዛዛቸው ሥር የነበረ ሠራዊት ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።
ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?
በበቀለም ጊዜ ቁመቱ አጭር፥ ሐረጉ ወደ እርሱ የሚመለስ፥ ሥሮቹም በበታቹ የነበሩት ሰፊ ወይን ሆነ፥ ወይንም ሆነ፥ ቅርንጫፎችን አበቀለ፥ ቅጠልም አወጣ።