በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ሕዝቅኤል 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሜዳ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በጌጦች አጌጥሽ፥ ጡቶችሽ አጐጠጐጡ፥ ጠጉርሽም አደገ፥ ሆኖም ዕርቃንሽንና ራቁትሽን ነበርሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜዳ ላይ እንዳለ ቡቃያ አሳደግሁሽ፤ አንቺም አደግሽ፤ ብርቅ ዕንቍ ሆንሽ። ጡቶችሽ አጐጠጐጡ፤ ጠጕርሽም አደገ፤ ነገር ግን ከእናትሽ ማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ነበርሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምቾት እንዳለው ተክል እንድታድጊ አደረግሁ፤ ቁመትና ጠንካራ ሰውነት በመጨመር አድገሽ የተዋብሽ ወጣት ሆንሽ፤ ጡትሽ አጐጠጐጠ፤ ጠጒርሽ ረዘመ፤ ነገር ግን እርቃንሽን ነበርሽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሻ ላይ እንደ አለ ቡቃያ አበዛሁሽ፤ አንቺም አደግሽ፤ ታላቅም ሆንሽ፤ በእጅጉም አጌጥሽ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ገባሽ፤ ጡቶችሽም አጐጠጐጡ፤ ጠጕርሽም አደገ፤ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆንሽ፤ ተራቍተሽም ነበርሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሻ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በእጅጉም አጌጥሽ፥ ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆንሽ፥ ተራቍተሽም ነበርሽ። |
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”
አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽ ላይ በዝንጉርጉር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ፥ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም።
በአንቺም በኩል አለፍሁ፥ በደምሽም ውስጥ ስትንፈራገጪ አየሁሽ። በደምሽ እንዳለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ፥ አዎን በደምሽ ውስጥ እያለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ።
“እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብጽ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብጽ በዙ።