ሕዝቅኤል 16:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በርኩሰቶችሽ ሁሉና በአመንዝራነትሽ ዕርቃንሽን ሆነሽ ተራቁተሽም በደምሽ ውስጥ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሺም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በእነዚህ አስጸያፊ ተግባሮችሽና አመንዝራነትሽ ሁሉ፣ ከእናትሽ ማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ሆነሽ በደምሽ ውስጥ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት የሕፃንነትሽ ወራት ትዝም አላለሽ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 እጅግ አጸያፊ በሆነ የአመንዝራነት ኑሮሽ የልጅነትሽን ሁኔታ አላስታወስሽውም፤ ይህም ማለት ራቁትሽን በደም ተነክረሽ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት ጊዜ ፈጽሞ ትዝ አላለሽም።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ከኀጢአትሽና ከዝሙትሽ ሁሉ ይህ ይከፋል፤ አንቺ ዕራቁትሽን ሳለሽ፥ ኀፍረትም ሞልቶብሽ ሳለሽ፥ በደምሽም ተለውሰሽ ሳለሽ፥ የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 በርኵስነትሽና በግልሙትናሽ ሁሉ ዕርቃንሽን ሆነሽ ተራቍተሽም ሳለሽ በደምሽም ተለውሰሽ ሳለሽ የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽም። Ver Capítulo |