ሕዝቅኤል 16:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ምክንያት ደስ የተሠኘሽባቸውን ወዳጆችሽን፣ የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከየአቅጣጫው ሁሉ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፤ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረተ ሥጋሽን ሁሉ ያያሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር የተደሰትሽባቸውን ማለት የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ ተጋልጠሽ ዕርቃንሽን ያዩ ዘንድ ከአካባቢው ሰብስቤ አንቺን በፊታቸው አራቊትሻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ እኔ ከአንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ የምትወጃቸውንም ከምትጠያቸው ጋር በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ ይከቡሻል፤ በእነርሱም ዘንድ ጕስቍልናሽን እገልጥብሻለሁ፤ ሁሉም ኀፍረትሽን ያዩብሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽ ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፥ በአንቺ ላይ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፥ ኅፍረተ ሥጋሽንም ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ። |
አንቺም የተደመሰስሽ ሆይ! ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኩል ተኩለሽ በተቆነጀሽ ጊዜ፥ በከንቱ እራስሽን ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ ረክሳለች፥ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፥ እርሷም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች።
ክፋትሽ ሳይገለጥ በፊት፤ አሁን ለአራም ሴቶች ልጆችና ለጎረቤቶችዋ ሁሉ፥ በዙሪያሽም ላሉት ለሚንቁሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንደ እርሷ መሰደቢያ ሆነሻል።
ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።