ሕዝቅኤል 11:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም፥ እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፥ እኔም በእስራኤል ድንበር እፈርድባችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤልም ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህች ከተማ ለእናንተ ሰታቴ አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጥዋ እንደ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፤ እኔም በእስራኤል ተራሮች እፈርድባችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፥ እኔም በእስራኤል ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። |
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገትዋ ላለባት ዝገትዋም ከእርሷ ላልወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቁራጭ ቁራጩን አውጣ፥ ዕጣ አልወደቀባትም።