ሕዝቅኤል 10:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መላ አካላቸው ሁሉ፥ ጀርባቸው፥ እጃቸው፥ ክንፋቸው፥ መንኰራኵሮቹም፥ የአራቱም መንኰራኵሮች፥ ዙሪያቸው በሙሉ በዐይኖች ተሞልተው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጀርባቸውን፣ እጃቸውን፣ ክንፋቸውን ጨምሮ መላ ሰውነታቸው እንዲሁም አራቱ መንኰራኵሮቻቸው በጠቅላላ በዐይን የተሞሉ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላ አካላቸውም ሆነ ጀርባቸው፥ እጆቻቸውም ሆኑ ክንፎቻቸው መንኰራኲሮቹ እንኳ ሳይቀሩ ሁሉም ብዙ ዐይኖች ነበሩአቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገላቸውም ሁሉ፥ ጀርባቸውም፥ እጆቻቸውም፤ ክንፎቻቸውም፥ መንኰራኵሮቹም፤ ለአራቱ የነበሩ መንኰራኵሮች በዙሪያቸው ዐይኖች ተሞልተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገላቸውም ሁሉ ጀርባቸውም እጃቸውም ክንፋቸውም መንኰራኵሮቹም፥ ለአራቱ የነበሩ መንኰራኵሮች፥ በዙሪያቸው ዓይኖች ተሞልተው ነበር። |
በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር።