ሕዝቅኤል 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሲሄዱም በአራቱም ጎናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም ነበር፥ ራስ ወደዞረበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 መንኰራኵሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜም ኪሩቤል ወደ ዞሩበት ወደ አራቱ አቅጣጫ ሁሉ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ኪሩቤል በሚሄዱበት ጊዜ መንኰራኵሮቹ ወዲያ ወዲህ አይሉም ነበር፤ ኪሩቤል በሚሄዱበት ጊዜ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ፣ ራስ ወደ ዞረበት ወደ ማንኛውም አቅጣጫ ይጓዙ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ወደ ፊታቸው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሳይዞሩ በቀጥታ ይሄዳሉ፤ የፊቱ መንኰራኲር ወደ የትኛውም አቅጣጫ ቢሄድ ሌሎቹ ሳይዞሩ በቀጥታ ይከተላሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ሲሔዱም በአራቱ ጎድናቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር፤ መጀመሪያው ወደሚያመለክትበት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ሲሄዱም በአራቱ ጐድናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር፥ ራሱ ወደምታመለክትበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር። Ver Capítulo |