ሕዝቅኤል 1:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወገቡ ከሚመስለው ወደ ላይ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል፥ ቤቱም በእሳት የተከበበ የሚመስል አየሁ፥ ወገቡ ከሚመስለው ወደ ታች ደግሞ በዙሪያው ብርሃን ያለው እሳት የሚመስል አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ በእሳት መካከል እንዳለ የጋለ ብረት፣ ከወገቡም በታች እሳት ይመስል እንደ ነበር አየሁ፤ ደማቅ ብርሃንም በዙሪያው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወገቡ ከሚመስለው ክፍል በላይ እሳት ውስጥ ገብቶ የጋለ ብረት የሚመስል ነገር ከወገቡም በታች እሳት የሚመስል ነገር አየሁ፤ የሚያንጸባርቅ ብርሃንም ዙሪያውን ገብቶበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ አምሳያ አየሁ፤ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት አምሳያ አየሁ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ አየሁ፥ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት ምስያ አየሁ፥ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ። |
እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስ መጣ፥ በዙሪያው ብርሃን ያለው መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበር፥ በእሳቱም መካከል የሚያንጸባርቅ ነገር ነበረ።
እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ።