Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕንባቆም 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጣ፤ ኀይሉም በዚያ ተሰውሯል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ብርሃኑ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው ኀይሉን ከሸፈነው እጁም የብርሃን ጮራ ይወጣል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፣ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፣ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፥ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፥ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።

Ver Capítulo Copiar




ዕንባቆም 3:4
14 Referencias Cruzadas  

በሚሄዱበትን መንገድ ልታበራላቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ መራሃቸው።


እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?”


ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፥ ሰማይንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፥


መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፥ በዙሪያውም ድንኳኑ፥ በውሃ የተሞሉ ጥቁር ደመናዎች ሸፍነውታል።


በቀንና በሌሊትም እንዲጓዙ፥ ጌታ ቀን በደመና ዓምድ መንገድ ሊመራቸው፥ ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ሊያበራላቸው ከፊታቸው ይሄድ ነበር።


በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤል ሰፈር መካከልም ገባ፤ ደመናና ጨለማ ነበረ፥ ሌሊቱን አበራ፤ ሌሊቱን ሙሉ ማንም አልቀረበም።


የጌታ ስም የጸና ግምብ ነው፥ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።


ወገቡ ከሚመስለው ወደ ላይ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል፥ ቤቱም በእሳት የተከበበ የሚመስል አየሁ፥ ወገቡ ከሚመስለው ወደ ታች ደግሞ በዙሪያው ብርሃን ያለው እሳት የሚመስል አየሁ።


እነሆ፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ድምጽ ነበር፥ ከክብሩ የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ለእርሱ ክብርና የዘለዓለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።


ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት፥ መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos