Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 1:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ዙፋን የሚመስል ነበረ፥ እርሱም የሰንፔር ድንጋይ ይመስል ነበር፥ ዙፋን በሚመስለው፥ በላዩ ላይም ሰው የሚመስል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ የሰንፔር ዙፋን የሚመስል ነገር ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የሰው መልክ የሚመስል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከጠፈሩም በላይ ሰንፔር ተብሎ ከሚጠራ ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር ተዘርግቶ ነበር፤ ሰው የሚመስልም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በራ​ሳ​ቸ​ውም በላይ ከአ​ለው ጠፈር በላይ የሰ​ን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል የዙ​ፋን አም​ሳያ ነበረ፤ በዙ​ፋ​ኑም አም​ሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አም​ሳያ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በራሳቸውም በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፥ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 1:26
34 Referencias Cruzadas  

ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤


ኃያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።


የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማያት የጠራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።


አንቺ የተሸገርሽ በአውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።


ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።


ከሕያዋኑ ራስ በላይ የሚያስፈራ፥ ሰማይ የሚመስል፥ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቅ፥ በራሳቸው ላይ ተዘርግቶ ነበር።


ከመካከልም አራት ሕያው ፍጡራን የሚመስሉ ወጡ። መልካቸውም እንደዚህ ነበረ፥ ሰውም ይመስሉ ነበር።


እኔም አየሁ፥ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ፥ ዙፋን የሚመስል ነገር ታየ።


ከቤቱ ውስጥ ሆኖ የሚናገረኝን ሰማሁ፥ በአጠገቤም ሰው ቆሞ ነበር።


እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ ማሳረፊያ ይህ ነው። የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ዳግመኛ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።


እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ።


እርሱ የጌታን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይጐናጸፋል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ መግባባት ይኖራል።


ቀኑንና ሰዓቱን አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ስለ ልጁ ግን፥ “አምላክ ሆይ! ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የጽድቅ በትር የመንግሥትህ በትር ነው።


የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።


እንግዲህ ከተናገርነው ነገር ዋናው ይህ ነው፦ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤


እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው።


እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።


ከዚያም አየሁ፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰው ልጅን የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።


ታላቅና ነጭ ዙፋን፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


እኔም ድል እንደ ነሣሁ፥ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።


በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “ውዳሴ ገናናነት ክብርም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos