ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ድምፅ መጣ፥ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ አደረጉ።
መንቀሳቀሳቸውን አቁመው ክንፎቻቸውን ዝቅ እንዳደረጉ፣ ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምፅ ተሰማ።
በራሳቸውም ላይ ካለው ጠፈር በላይ ድምፅ ተሰማ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ይሰበስቡ ነበር።
በራሳቸውም ላይ ካለው ጠፈር በላይ ድምፅ ተሰማ፥ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።
ከሕያዋኑ ራስ በላይ የሚያስፈራ፥ ሰማይ የሚመስል፥ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቅ፥ በራሳቸው ላይ ተዘርግቶ ነበር።
እኔም አየሁ፥ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ፥ ዙፋን የሚመስል ነገር ታየ።