Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 1:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኆች ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ፥ እንደ ማዕበል ድምፅ፥ እንደ የታላቅ ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የክንፎቻቸውን ድምፅ ሰማሁ፤ ድምፁም እንደሚጐርፍ ውሃ ጩኸት፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ድምፅና እንደ ሰራዊት ውካታ ነበር። መንቀሳቀሳቸውን ሲያቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24-25 በሚበርሩበትም ጊዜ ክንፎቻቸው ሲጋጩ ሰማሁ፤ ድምፁም የባሕር ማዕበል ጩኸትና የታላቅ ሠራዊት ሁካታ፥ እንዲሁም የሁሉን ቻዩን የእግዚአብሔርን ድምፅ ይመስል ነበር፤ መብረራቸውን ባቆሙ ጊዜ ክንፎቻቸውን ያጥፉ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምፅ ተሰማ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሲሄ​ዱም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራ​ዊ​ትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆ​ሙም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል የአምላክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅም ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፥ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 1:24
12 Referencias Cruzadas  

ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።


የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጉርምርምታ አድምጡ።


በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።


የምድር ነገሥታት፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ለጌታም ዘምሩ።


ሁሉን የሚችል አምላክ ሲናገር እንደሚያሰማው ዓይነት ድምፅ የኪሩቤል ክንፎች ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ ተሰማ።


ይህም የሕያዋኑ ክንፎች እርስ በእርሳቸው ሲማቱ የሚወጣው ድምፅ፥ በአጠገባቸውም የነበሩት የመንኰራኵሮች ድምፅ ነበር፥ እርሱም ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ነበር።


እነሆ፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ድምጽ ነበር፥ ከክብሩ የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።


እግሮቹም በምድጃ ውስጥ የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውሃዎች ድምፅ ነበረ።


የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos