ዘፀአት 9:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውና ነጎድጓዱ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ ኃጢአትን ጨመረ፥ እርሱና አገልጋዮቹም ልባቸውን አደነደኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ባየ ጊዜ እንደ ገና በደለ፤ እርሱና ሹማምቱ ልባቸውን አደነደኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ግን ዝናቡ፥ በረዶውና ነጐድጓዱ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ እርሱና መኳንንቱ ልባቸውን በማደንደን እንደገና ኃጢአት ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውም፥ ነጐድጓዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደልን ጨመረ፤ እርሱና ሹሞቹም ልባቸውን አደነደኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዝናቡ በረዶውም ነጎድጓዱም እንደ ተቍረጠ ባየ ጊዜ ኃጢያትን ጨመረ፤ እርሱና ባሪያዎቹም ልባቸውን አደነደኑ። |
ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።
ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።
ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?