ዘፀአት 9:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በትሩን ወደ ሰማያት ዘረጋ፤ ጌታም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፥ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ ጌታም በግብጽ ምድር ላይ በረዶ አዘነበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ ባነሣ ጊዜ እግዚአብሔር ነጐድጓድና በረዶ አወረደ፤ መብረቅም በምድሪቱ ላይ ሆነ። እግዚአብሔር በግብጽ ምድር በረዶ አዘነበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ በትሩን አንሥቶ ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ መብረቅም ወደ ምድር አወረደ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ላይ በረዶን አዘነበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ ሀገር ሁሉ ላይ በረዶ አዘነበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ላይ በረዶ አዘነበ። |
እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
እነሆ እኔ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ፥ ከተመሠረተች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ከባድ በረዶ አዘንባለሁ።
በረዶና እሳት ነበረ፥ በበረዶውም መካከል እጅግ ከባድ የሚበርቅ እሳት ነበር፥ በግብጽ ምድር ሁሉ አገር ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ሆኖ አያውቅም።
ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል።
በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍና የበረዶ ድንጋይ፥ እሳትና ዲን በእርሱና በወታደሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉት ብዙ ሕዝቦች ላይ አዘንባለሁ።
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ የቤትሖሮንን ቁልቁለት በመውረድ ላይ ሳሉ፥ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ ጌታ ከሰማይ ታላላቅ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ነውጡ እጅግ ትልቅ ነበር።
በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነበርና።
የፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።