La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም ልከህ ከብቶችህንና በሜዳ ያለ የአንተ የሆነውን ሁሉ አምጣ፤ በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንሰሳ ሁሉ ላይ በረዶ ይወርዳል እነርሱም ይሞታሉ።’”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከብቶችህና በመስክ ላይ ያለህ ማንኛውም ነገር ወደ መጠለያ ይገቡ ዘንድ አሁን ትእዛዝ ስጥ፤ ምክንያቱም በረዶው ወደ መጠለያ ባልገቡትና በመስክ ላይ በቀሩት በማንኛውም ሰውና እንስሳት ላይ ወርዶባቸው ስለሚሞቱ ነው።’ ”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁንም በመስክ የተሰማሩት እንስሶችህና በዚያ ያለው ንብረትህ ሁሉ ወደ መጠለያ እንዲጠጋ ትእዛዝ ስጥ፤ ወደ ቤት ያልገቡ ሰዎችም ሆኑ እንስሶች ቢኖሩ ግን በበረዶው ስለሚመቱ ሁሉም ያልቃሉ።’ ”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁን እን​ግ​ዲህ ፥ ከብ​ቶ​ች​ህ​ንም በሜ​ዳም ያለ​ህን ሁሉ ፈጥ​ነህ ሰብ​ስብ። በሜዳ የተ​ገኘ ወደ ቤት ያል​ገባ ሰውና እን​ስሳ ሁሉ በረዶ ወር​ዶ​በት ይሞ​ታ​ልና።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንሰሳ ሁሉ በረዶ ወርዶበት ይሞታልና አሁን እንግዲህ ላክ፤ ከብቶችህንም በሜዳም ያለህን ሁሉ አስቸኵል።’”

Ver Capítulo



ዘፀአት 9:19
5 Referencias Cruzadas  

እንስሶቻቸውን ለበረዶ፥ ሀብታቸውንም ለመብረቅ ሰጠ።


በረዶውም በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ ያለውን ሁሉ ከሰው እስከ እንስሳ መታ፤ የእርሻን ቡቃያ መታ፥ በረዶውም የአገሩን ዛፍ ሁሉ ሰበረ።


ጌታም ያንን ነገር በማግስቱ አደረገ፥ የግብጽም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእስራኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አልሞተም።


የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ስላልተጠነቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ቢጠነቀቅ ኖሮ ነፍሱን ባዳነ ነበር።


ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።