ዘፀአት 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ጌታ ሙሴን እንደ ተናገረው ፈርዖን አልሰማቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረውም፣ ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አሁንም እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ በማደንደን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሙሴ እንደ ተናገረ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አላደመጣቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እግዚአብሔርም ለሙሴና ለአሮን እንደ ተናገረው አልሰማቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም። |
ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብጽ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ ተመልከት በፈርዖንም ፊት ታደርጋቸዋለህ፤ እኔም ልቡን አጸናዋለሁ፥ ሕዝቡንም አይለቅቅም።
ፈርዖንም እናንተን አይሰማችሁም፥ እጄንም በግብጽ ላይ አደርጋለሁ፥ ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች፥ በታላቅ የፍርድ ሥራ ከግብጽ ምድር አወጣለሁ።
ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ፥ እንዲያጠፉአቸው ምሕረትንም ሳያደርጉ ፈጽመው እንዲፈጅዋቸው፥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ልባቸውን እንዲያደነድኑ ከጌታ ዘንድ ሆነ።