ዘፀአት 39:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቋድ እንደ እርሱ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ፥ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥበብ የተፈተለው መታጠቂያ በተመሳሳይ መልክ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከኤፉዱ ጋራ አንድ ወጥ የሆነና ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር የተሠራ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከወርቅ ክር፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና፥ ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ በብልኀት የተጠለፈው ቀበቶ አንድ ወጥ በመሆን ከኤፉዱ ጋር ተያይዞ ተሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እርስዋን ከወርቅ፥ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም፥ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም እንደ ሠሩ የልብሰ መትከፉን ቋድ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቍድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ነበረ፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ። |
በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን።
ልብሶቹን ወስደህ ለአሮን እጀ ጠባቡን፥ የኤፉዱን መደረቢያ፥ ኤፉዱንና የደረት ኪስ ታለብሰዋለህ፥ በብልሃትም የተጠለፈ ኤፉድ ታስታጥቀዋለህ፤
ልብስም አለበሰው፥ በመርገፍም በተጌጠ ዝናር አስታጠቀው፥ ቀሚስም አለበሰው፥ ኤፉድም ደረበለት፥ በብልሃትም በተጠለፈ የኤፉድ ማንጠልጠያ አስታጠቀውና በእርሱ ላይ ኤፉዱን አሰረው።