አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።
ዘፀአት 39:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት የወርቅ ፈርጦችና ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረቱ ኪስ በሁለቱ በኩል አደረጉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ቀለበቶቹን ከደረት ኪሱ ሁለት ጐኖች ጋራ አያያዟቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት የወርቅ ፈርጦችና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችም ሠርተው፥ ሁለቱን ቀለበቶች በደረት ኪሱ በላይ በኩል ካሉት ማእዘኖች ጋር አያያዙአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለትም የወርቅ ፈርጦች፥ ሁለትም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ ሁለቱንም የወርቅ ቀለበቶች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለትም የወርቅ ፈርጦች፥ ሁለትም የወርቅ ቀለበቶች ሠሩ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረቱ ኪስ በሁለቱ ወገን አደረጉ። |
አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።