ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዓታቸው ዘወትር በየቀኑ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየተወሰኑትም በዓላት፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል በየዳሱም በዓል ቁርባን ያቀርቡ ነበር።
ዘፀአት 34:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰባቱን ሱባዔ በዓል ትጠብቃለህ፥ እርሱም የስንዴ መከር በኵራት ነው፤ በዓመቱም መጨረሻ የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰባቱን ሱባዔ የመከር በዓል ከስንዴው መከር በኵራት ጋራ፣ እንዲሁም የመክተቻ በዓልን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አክብር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የስንዴአችሁን በኲራት በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከርን በዓል አክብሩ፤ የዓመቱ መጨረሻ በሆነው በፍሬ መከር ጊዜ የዳስን በዓል አክብሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፤ እርሱም የስንዴ መከር መጀመሪያ ነው፤ በዓመቱም መካከል የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፥ እርሱም የስንዴ መከር በኵራት ነው፤ በዓመቱም ፍጻሜ የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ። |
ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዓታቸው ዘወትር በየቀኑ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየተወሰኑትም በዓላት፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል በየዳሱም በዓል ቁርባን ያቀርቡ ነበር።