ሑራም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ጥልቀት፥ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የክብ ማእከል ርዝመት፤ ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ።
ዘፀአት 30:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የመታጠቢያ ሳሕንና መቀመጫውን ከነሐስ ሥራ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል ታኖረዋለህ፥ ውኃም ትጨምርበታለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለመታጠቢያ ከንሓስ ማስቀመጫው ጋራ የንሓስ መቆሚያ አብጅ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠህ ውሃ አድርግበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መታጠቢያ ገንዳ ከነሐስ ሠርተህ፥ እግሮች ባሉት ከነሐስ በተሠራ የሳሕን መቀመጫ ላይ አኑረው፤ እርሱንም በመሠዊያውና በድንኳኑ መካከል አድርገህ ውሃ ጨምርበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የመታጠቢያ ሰን ከናስ፥ መቀመጫውንም ከናስ ሥራ፤ በምስክሩ ድንኳንና በመሠዊያው መካከል ታኖረዋለህ፤ ውኃም ትጨምርበታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመታጠቢያ ሰንና መቀመጫውን ከናስ ሥራ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል እርሱን አድርገህ ውኃን ትጨምርበታለህ። |
ሑራም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ጥልቀት፥ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የክብ ማእከል ርዝመት፤ ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ።
ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎችን ሠራ፤ እያንዳንዱም ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር።
እንዲሁም ንጉሡ ዐሥር የመታጠቢያ ሳሕኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበውን ነገር ሁሉ እንዲያጥቡበት አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኩሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትቸኩል፥ ልብህም በእግዚአብሔር ፊት ቃልን ለመናገር አይቸኩል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።