Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 30:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “መታጠቢያ ገንዳ ከነሐስ ሠርተህ፥ እግሮች ባሉት ከነሐስ በተሠራ የሳሕን መቀመጫ ላይ አኑረው፤ እርሱንም በመሠዊያውና በድንኳኑ መካከል አድርገህ ውሃ ጨምርበት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ለመታጠቢያ ከንሓስ ማስቀመጫው ጋራ የንሓስ መቆሚያ አብጅ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠህ ውሃ አድርግበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “የመታጠቢያ ሳሕንና መቀመጫውን ከነሐስ ሥራ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል ታኖረዋለህ፥ ውኃም ትጨምርበታለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰን ከናስ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ከናስ ሥራ፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ውኃም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የመታጠቢያ ሰንና መቀመጫውን ከናስ ሥራ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል እርሱን አድርገህ ውኃን ትጨምርበታለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:18
15 Referencias Cruzadas  

ሑራም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ጥልቀት፥ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የክብ ማእከል ርዝመት፤ ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ።


ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፤ እያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር፤


እንዲሁም ጥልቀቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ አጋማሽ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር፥ ዙሪያው ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ክብ ገንዳ አሠራ፤


ሰሎሞን ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎችን አሠርቶ፥ አምስቱን በቤተ መቅደሱ ደቡባዊ ጐን የቀሩትን አምስቱን ደግሞ በቤተ መቅደሱ ሰሜናዊ ጐን አኖራቸው፤ እነዚህ ገንዳዎች ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚታረድ እንስሳ ሥጋ ሁሉ የሚታጠብባቸው ነበሩ፤ በትልቁ ገንዳ ያለው ውሃ ደግሞ ለካህናቱ መታጠቢያ የሚውል ነበር።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያና ለእርሱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ፥ የመታጠቢያው ሳሕንና ማስቀመጫው፥


የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን ጭምር ከነሐስ ሠራ፤ ነሐሱም የተገኘው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ የሚያገለግሉ ሴቶች ካመጡት የነሐስ መስተዋቶች ነው።


የመታጠቢያውን ሣሕን በድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠህ ውሃ ሙላበት።


ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትገባበት ጊዜ ለአረማመድህ ጥንቃቄ አድርግ፤ እዚያ ሄዶ ደጉን ከክፉ ለይተው የማያውቁ ሞኞች ሰዎች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ የምክር ቃላትን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ መገኘት ይበልጣል።


ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ይሆኑ ዘንድ በመሠዊያውና ለእርሱ መገልገያ በተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በመታጠቢያው ሳሕንና በሳሕኑ ማስቀመጫ ላይ ረጨ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን ራሱ በምሕረቱ አዳነን፤ ያዳነንም በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በተገኘው መታደስ ነው።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንኖር እርስ በርሳችን አንድነት ይኖረናል። ደግሞም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos