ዘፀአት 28:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የፍርዱን የደረት ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራው ሥራው፤ እንደ ኤፉዱ አሠራር ሥራው፤ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ ሥራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የፍርድ መስጫውን የደረት ኪስ ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው አድርገህ አብጀው፤ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ አብጀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጠየቅበትን የደረት ኪስ ለሊቀ ካህናቱ ሥራ፤ አሠራሩ እንደ ኤፉድ ሆኖ በተመሳሳይ ጥልፍ ያጌጠ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን ልብሰ እንግድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መትከፍም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍታም ሥራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን የደረት ኪስ ሥራው እንደ ኤፉዱም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከጥሩ በፍታም ሥራው። |
“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።
በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፥ በጌታ ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በጌታ ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።
የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ የተጠለፈ እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያና መታጠቂያ፤ ካህን እንዲሆንልኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ የተቀደሰ ልብስ ይሥሩላቸው።
ልብሶቹን ወስደህ ለአሮን እጀ ጠባቡን፥ የኤፉዱን መደረቢያ፥ ኤፉዱንና የደረት ኪስ ታለብሰዋለህ፥ በብልሃትም የተጠለፈ ኤፉድ ታስታጥቀዋለህ፤