Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 28:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጠየቅበትን የደረት ኪስ ለሊቀ ካህናቱ ሥራ፤ አሠራሩ እንደ ኤፉድ ሆኖ በተመሳሳይ ጥልፍ ያጌጠ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “የፍርድ መስጫውን የደረት ኪስ ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው አድርገህ አብጀው፤ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ አብጀው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “የፍርዱን የደረት ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራው ሥራው፤ እንደ ኤፉዱ አሠራር ሥራው፤ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ ሥራው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ የፍ​ር​ዱን ልብሰ እን​ግ​ድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መት​ከ​ፍም አሠ​ራር ሥራው፤ ከወ​ር​ቅና ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍ​ታም ሥራው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን የደረት ኪስ ሥራው እንደ ኤፉዱም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከጥሩ በፍታም ሥራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:15
11 Referencias Cruzadas  

መረግድ፥ (ቅጠልያ ዕንቊ) በሊቀ ካህናቱ ኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚደረግ ፈርጥ፥


“እንዲሁም የተቀደሰውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች አብጀው፤ በእነርሱም ላይ ኪሩቤል በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ።


“ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ አድርግለት።


እንደ ገመድ ተጐንጒነው ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ሁለት ድሪዎችንም አበጅተህ ከሁለቱ ፈርጦች ጋር እንዲያያዙ አድርግ።


ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሳንቲ ሜትር የጐኑም ስፋት ኻያ ሁለት ሳንቲ ሜትር ሆኖ ታጥፎ የተደረበ ትክክል አራት ማእዘን ይሁን።


ዑሪምና ቱሚም የተባሉትን ነገሮች በደረት ኪሱ ውስጥ ታስገባቸዋለህ፤ አሮንም ወደ ቅዱሱ ድንኳን ሲገባ በደረት ኪሱ ተሸክሞአቸው ይግባ፤ የእኔን ፈቃድ ለእስራኤል ሕዝብ ማስታወቅ ይችል ዘንድ በፊቴ ለማገልገል በሚገባበት ጊዜ ሁሉ በደረት ኪሱ ያድርጋቸው።


በዐይነት የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ በጥልፍ ያጌጠ ሸሚዝ፥ ጥምጥምና መታጠቂያ፤ ወንድምህ አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ እነዚህን የተቀደሱ ልብሶች ይሥሩላቸው።


“ኤፉድንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ ከቀይ ከፈይ ከወርቅ ምዝምዝና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አስጊጠው ይሥሩ።


ከዚህ በኋላ አሮንን የክህነት ልብስ አልብሰው፤ ሸሚዙን፥ ኤፉዱን፥ የኤፉዱን መደረቢያ ቀሚስ፥ የደረት ኪሱን አልብሰው፤ መታጠቂያውን አስታጥቀው፤


በኤፉዱም ላይ የደረት ኪስ ሰፍቶ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚገለጥባቸውን ኡሪምና ቱሚምን አኖረ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos