ዘፀአት 23:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጠላለሁ፥ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚናገረውን በጥንቃቄ ብታደምጥና ያልኩህን ሁሉ ብታደርግ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህን እቃወማለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱ ብትታዘዝና እኔ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም ጠላቶችህን እጠላለሁ፤ ተቃዋሚዎችህንም እዋጋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን ቃሌን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጥላቸዋለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋልሁ። |
ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ ጌታ ሆይ የገዛኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ በኃይልህ ታላቅነት፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፥ እንደ ድንጋይ ቀጥ አሉ።
እግዚአብሔርም ከግብጽ አውጥቶታል፤ ጉልበቱ አንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።
እንደ አንበሳ ዐርፎ ተኝቶአል፥ እንደ እንስቲቱም አንበሳ ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚባርክህ ሁሉ የተባረከ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተረገመ ይሁን።”
“ለጌታ እግዚአብሔር ፍጹም ብትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙን ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቅ፥ ጌታ እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያን እንዲህ አሉአቸው፦ “ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ እንደሆነ እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን?”