ዘፀአት 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ ቂጣ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስከ ንጋት ድረስ አይቆይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የመሥዋዕትን ደም እርሾ ካለበት ነገር ጋራ አድርገህ ለእኔ አታቅርብ። “የበዓል መሥዋዕቴ ስብ እስከ ንጋት ድረስ አይቈይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንስሳ በምትሠዉልኝ ጊዜ እርሾ የነካው እንጀራ መባ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ በእነዚህ በዓላት የሚሠዉት እንስሶች ስብ ለሚቀጥለው ቀን አይትረፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ እንጀራ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስኪነጋ አይደር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ እንጀራ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስኪነጋ አይደር። |
ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።
“ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን።
የሚያቀርውም ለምስጋና ቢሆን፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ እርሾ ያልነካው በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል።
በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቆይ አታድርግ።