ጉዳት ቢደርስባት ግን ሕይወት ስለ ሕይወት፥
ነገር ግን የከፋ ጕዳት ቢደርስ ሕይወት በሕይወት፣
ነገር ግን ሴትዮዋ ራስዋ ብርቱ ጒዳት የደረሰባት ከሆነች ቅጣቱ ‘በሕይወት ምትክ ሕይወት፥
ተሥዕሎተ መልክእ የተፈጸመለት ፅንስ ቢያስወርዳት ግን ሕይወት በሕይወት፥
ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፥
ሰውም ባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት።
በስብራት ፋንታ ስብራት፥ በዐይን ፋንታ ዐይን፥ በጥርስ ፋንታ ጥርስ ይሁን፤ በሰው ላይ ጉዳት ያደረገ ሰው እንዲሁ ይደረግበት።
ሞት የተፈረደበትን ነፍሰ ገዳዩንም ለማዳን የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
ዓይንህም አትራራለት፥ ሕይወት በሕይወት፥ ዐይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ ይመለስ።”