አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
ዘፀአት 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው በተንኰል ሆነ ብሎ ሌላውን ቢገድል፣ ከመሠዊያዬ ተወስዶ ይገደል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ሰው በቊጣ ተነሣሥቶና ሆን ብሎ ሌላ ሰው ቢገድል፥ ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ግን ቢሸምቅ ጠላቱንም በተንኰል ቢገድለውና ቢማፀን፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውን በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲሞት ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው። |
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር አለቆቹን “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርሷን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል” ሲል አዘዛቸው።
ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።”
ይልቁንም በርኩስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን፥ ጌትነትንም የሚንቁትን፤ ደፋሮችና እምቢተኞች ስለ ሆኑ ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይፈሩም፤