ዘፀአት 20:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃፍረተ ሥጋህ በእርሱ ላይ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ።’” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ መሠዊያዬም በደረጃ አትውጣ፤ አለዚያ ኀፍረተ ሥጋህ ይገለጣል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀፍረተ ሥጋችሁ በእርሱ ላይ እንዳይገለጥ በመወጣጫ መሰላል አትውጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀፍረተ ሥጋህ በእርሱ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃፍረተ ሥጋህ በእርሱ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ። |
ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትቸኩል፥ ልብህም በእግዚአብሔር ፊት ቃልን ለመናገር አይቸኩል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።
የእርከኑም ርዝመት ዐሥራ አራት ክንድ ወርዱም ዐሥራ አራት ክንድ ነው፥ አራቱም ማዕዘን እኩል ነው፤ በዙሪያውም ያለው ጠርዝ ግማሽ ክንድ ነው፥ የመሠረቱም ዙሪያ አንድ ክንድ ነው፤ ደረጃዎቹ ወደ ምሥራቅ ይመለከታሉ።
ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።