ዘፀአት 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይትሮም ጌታ ለእስራኤል ስላደረገው መልካም ነገር ሁሉ፥ ከግብጽም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮቶርም እግዚአብሔር እነርሱን ከግብጻውያን እጅ በመታደግ ለእስራኤል ያደረገውን በጎ ነገር ሁሉ በመስማቱ ተደሰተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የትሮም ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ እግዚአብሔር ከግብጻውያን እጅ እስራኤልን ለማዳን ስላደረጋቸው መልካም ነገሮች ደስ ተሰኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮቶርም እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ እንደ አዳናቸው ሰምቶ በሁሉ አደነቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው። |
ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።
ጌታ ስላደረገልን ሁሉ፥ የጌታን ቸርነትና የጌታን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን የተትረፈረፈ ጽኑ ፍቅር እናገራለሁ።
እናንተ የምትወዷት ሁሉ፥ ከኢየሩሳሌም ጋር ሐሤትን አድርጉ፤ ስለ እርሷም ደስ ይበላችሁ፤ እናንተም የምታለቅሱላት ሁሉ፥ ከእርሷ ጋር በደስታ ሐሤትን አድርጉ፤
እርሱም ቄናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።